Visitors Counter

  15286
  Today45
  Yesterday49
  This_Week171
  This_Month762
  All_Days15286

  መዘከርታ

  የሰሲና 421 ታሪክ ሲታወስ

   

  የ ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ሰራዊት ሃገሪቱን በሞላ እየተቆጣጠረ ወደ ርእሰ መዲናችን አዲስ አበባ እየተጠጋ በመጣበት ወቅት የ ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ መሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ፣ ስዩም መስፍን በውድቀቱ ዋዜማ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በግንቦት 1983 ዓ/ም ለድርድር ከቀረበው ደርግ ተዘጋጅተው ነበር፡፡
  ይሁን እንጂ የደርግ ሰራዊት እጅግ ፈጣን በሆነ መልኩ እየፈረሰ ነበር፡፡ በተቃራኒው የ ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ሰራዊት ድል በድል እየተጎናፀፈ ነበር፡፡ ሁኔታዎች በዚህ መልኩ እያሉ የ ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ አመራር የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን ድርድርን እየመሩ እያሉ መሪዎች ለድርድር ከኛ ጋር የተቀመጡት የደርግ ልዑካን ሰራዊታቸው እየተበተነና ለኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ሰራዊት እጁ እየሰጠ መሆኑን ገለፀላቸው፡፡ ከዚህ ቦኃላ አቶ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን በለንደን ከተማ ሆነው አሁን በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት መግለጫ ሰጡ፡፡ ይህ መግለጫም የዓለም መገናኛ ብዙሃን ማሰራጨት ጀመሩ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን መሃል አገር ውስጥ ካሉት የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች በስልክ በመነጋገር እያሉ አዲስ አበባ የነበሩት የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች አቶ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን በፍጥነት ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ጠየቋቸው፡፡
  በዚህ ወቅት ወደ አገር ቤት የሚመለሱበት ሁኔታ አስመልክቶ መነጋገር ጀመሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ እያሉ እኚህ መሪዎች ወደ አረፉበት ሆቴል አንድ አልፋታሕ እርዋ የተባለ ሱዳናዊ እንኳን ደስ አላቹሁ ሊላቸው መጣ፡፡
  ይህ ሱዳናዊ አልፋትሕ እርዋ የሱዳን መንግስት የደህንነትና የፀጥታ ሓላፊ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ወዳጅና የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ደጋፊ ነበረ አቶ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን ይህን ሰው ባገኙት ግዜ ወደ ሃገር ቤት በተሎ ሰለ መመለስ አጫወቱት፡፡
  ከዚህ ቦኃላ አልፋትሕ አንድ መፍትሄ አመጣ ከለንድን ወደ ሱዳን አብረው እንዲሄዱና ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በግል ኣውሮፕላን ወደ አዲስ አባባ መብረር እንደሚችሉ ገለፀላቸው እነሱም በዚህ ሃሳብ ተስማሙ፡፡
  መለስ፣ ስዩምና አልፋትሕ እርዋን ከለንደን ተነስተው ካርቱም ደረሱ፡፡ በካርቱም የአልፋትሕ እርዋ ሰሲና 421 ጎልደን ኤግል 3 የተባለች አውውሮፕላን ተዘጋጅታ ጠበቀቻቸው በዚህች አውሮፕላን ተሳፍረው ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ቀጠሉ፡፡ መለስ፣ ስዩምና አልፋትሕ እርዋ ከለንደን ወደ ሱዳን ሲጓዙ ሌላ ሰው አልነበራቸውም፡፡ ከሱዳን ሲጓዙ ግን ሌሎች ተጨመሩባቸው እነሱም
  1. ታጋይ ፍስሃ አፈወርቂ
  2. ታጋይ አባዲ ዘሞ
  3. ታጋይ ተፈራ ዋልዋ
  4. ሲዳናዊ ፓይለት አብደል ሓሚድን
  5. አልፍሬ ዓሊ ሚራሕ ነበሩ ፡፡

   

  ስለዚህ ይህች ትንሽ አውሮፕላን መለስ፣ ስዮምና አልፋታሕን ጨምራ ስምንት ሰዎች ይዛ ነው በራራ የጀመረችው፡፡ የዚህች አውሮፕላን ዋና አብራሪ ሱዳናዊ ሲሆን ረዳት አብራሪው አልፋትሕ ኣርዋ ነበረ፡፡
  ጉዞው ከካርቱም በሑመራ በኩል ነበረ አጀማመሩም በደህና መልካምና ነበረ፡፡ አዲስ አበባ ያሉ መሪዎች ደግሞ ይህችን አውሮፕላን መድረስዋን እየተጠባበቁ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት በረራው አቋርጦ የነበረበት ወቅት በመሆኑ ማንኛውም የአውሮፕላን እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ይህች ትንሽ ከሱዳን የምትነሳው አውሮፕላን ከሳምንታት በኃላ ለመጀመርያ ግዜ ነበር በቦሌ አየር ማረፍያ የምታርፈው፡፡
  ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ አመራሮች ይህች አውሮፕላን በምታርፍበት ወቅት አደጋ እንዳያጋጥም አስፈላጊው ጥንቃቄ በማድረግ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ለደህንነት ሲባልም የኢትዮጵያ አየር መንግድ ሰራተኞች ይህች አውሮፕላን ከ ኬንያ ናይሮቢ የተነሳች እና የእርዳታ ሰራተኛች ይዛ የምትመጣ መሆንዋን ተነገሯቸዋል፡፡ ይህች ከካርቱም የተነሳችው ትንሽ አውሮፕላን ግን በመንገድ ላይ ሌላ ያልተጠበቀ አደጋ አጋጠማት በሰማይ ላይ እያለች የሞተር ነዳጅ የሚያስተላልፈው መስመር ድንገት በመዘጋቱ የቀኝ ሞተር መስራት አቆመ አብራሪው በበረራው ላይ አደጋ ተጋረጠ፡፡ በዚህም ምክንያት በአውሮፕላኑ በነበሩት ተሳፋሪዎች ትልቅ አደጋ አጠላባቸው፡፡ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ እና አልፋትሕ በድንጋጤ ላብ በላብ ሆኑ፡፡ የሚዙትና የሚጨብጡት ኣጡ፡፡ ተሳፋሪዎችም በሁኔታው እጅግ ተደናገጡ፡፡ ይህች አውሮፕላን ወደ መሬት ትወድቃለች የሚል ስጋት በሁሉም ላይ ነገሰ ብዙ ሳይቆይ ግን እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ ያለን ተዘግቶ የነበረው መስመር በራሱ በመከፈቱ ቆሞ የነበረው የአውሮፕላኑ የቀኝ ሞተር ተነስቶ ስራ ጀምሯውል ካሁን ቦኃላ ሊገጥመን የሚችል ምንም ችግር የለም አዲስ አበባ እናርፋለን የሚል መልካም ዜና ከአልፋትሕ እርዊ ተሰማ፡፡
  በአውሮፕላኑ የነበረው ፍርሃትና ስጋት በአንዴ ተገፈፈ ሁሉም በደስታ አንጨበጨቡ፡፡ ከጥቂት ግዜ ጉዞ በኃላ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፍያ ደረሱ፡፡ ታወሩ ተከፈተ አውሮፕላንዋም በሰላም አረፈች፡፡
  በቦሌ አየር ማረፍያ የነበሩት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ አመራሮች በአውሮፕላንዋ የመጡትን ተጋይ ጓደኞቻቸው በደስታ ተቀበልዋቸው፡፡
  በአውሮፕላንዋ የነበሩት
  1. መለስ ዜናዊ
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ታጋይ
  • ነባር አመራር ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ አመራር
  • የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ሊቀ ወንበር
  • የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩ
  2. ስዩም መስፍን
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት መስራች
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ታጋይ
  • ነባር አመራር ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ አመራር
  • የ ህ.ወ.ሓ.ት ምክትል ሊቀ ወንበር
  • እስከ የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት የደረሰ
  3. አባዲ ዘሞ
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ታጋይ
  • ነባር አመራር ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ አመራር

  4. ፍስሃ አፈወርቂ
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ታጋይ
  • የሃገሪቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት
  • እስከ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ የደረሰ
  5. ተፈራ ዋልዋ
  • ነባር የ ህ.ወ.ሓ.ት \ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ\ ታጋይ
  • እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት የደረሰ
  6. አልፋትሕ እርዋ \ሱዳናዊ\
  7. አልፍሬ ዓሊ ምራሐ
  8. ሱዳናዊ ፓይለት አብዱል ሓሚድ

  Recalling the history of CESSNA 421


  By the time the EPRDF troop approached full occupation of the capital, Addis Ababa, a peace talk was arranged to take place in May 1991 G.C. in London between leaders of the EPRDF and representatives of the Dergue Regime, a regime which was on the brink of collapse. Hence, EPRDF leader Meles Zenawi and Seyoum Mesfin availed in London for the peace talk.
  Meanwhile, the Dergue troop started to fall apart while the EPRDF troop progressed victoriously.
  EPRDF lead persons Meles and Seyoum dealt this issue to the organizers of the peace talk and explained the falling apart of the Dergue troop and that the government is collapsing. With this, they questioned the necessity of the peace talk. As a result, the peace talk was cancelled.
  While in London, Meles and Seyoum declared to global media that the EPRDF will bring all political parties to the scenario and realize and representative transitional government.
  Due to the victorious progress of the EPRDF troop, communications between Meles and Seyoum in London and the EPRDF leadership in land demanded indicated the need for immediate return of Meles and Seyoum to the Capital Addis. Meles and Seyoum started to deal on how to get back to Ethiopia immediately. It is at this time they met a long time friend, supporter of the armed struggle against the Dergue, Intelligence and Security Chief of Sudan , Sudanese General Elfatih Erwa. Al Fatah expressed his happiness on the victories. Meles and Seyoum thanked Elfatih and discussed their urgent need to return to Ethiopia. Elfatih Proposed that, he joins them in a flight to Khartoum and that they fly from Khartoum to Addis in his private. They all agreed on the proposal. Meles, Seyoum and Elfatih Erwa reached Khartoum and took off for Addis Ababa, in the CESSNA 421 GOLDEN EAGLE III aircraft, this time with five more passengers on board. The other five were;

  1.  Freedom fighter Fesseha Afewerki
  2.  Freedom fighter Abadi Zemo
  3.  Freedom fighter Tefera Walewa
  4.  Al Fre Ali Mirah and
  5.  Abdel Hamid Pilot

  A Sudanese Capitain was operating the small aircraft while General Elfatih Erwa was the copilot. Members of the EPRDF leadership, in Addis Ababa, Bole Airport, eagerly await the arrival of the aircraft, the airport, due to the unstable conditions was not in service. If successful, the landing of the CESSNA is going to be the first one in many weeks.
  All precautions were taken for a better landing of the CESSNA at ground. For security matters, the workers at the bole international Airport were informed that the CESSNA has aid workers on board and that it departed from Nairobi, Kenya.
  While on air a dangerous situation prevailed. The aircraft went into a deadly situation because of a malfunctioning gas line at the right wing engine. The right wing engine failed. This shed the spirit of fear and death. The captain and the copilot got shocked. All passengers knew what was going on and were all sure that they will shortly lose height and crash. This created the worst tension that can happen in flights.
  Moments later, the passengers heard the following words of General Elfatih, "Congratulations! Congratulations! Congratulations! The gas passage is open now. It is functioning well. We are safe! We are safe! We shall land in Addis nice and safe! "
  The tension inside the aircraft was cleared. All passengers expressed the happy feelings by clapping. After some hours of flight, the CESSNA landed at bole international Airport in Addis Ababa. The passengers were welcomed by the awaiting members of leadership of EPRDF at Bole.
  The passengers and crew in the CESSNA were;
  1. Meles zenawi
  Freedom Fighter TPLF/EPRDF
  Long time leader of TPLF/EPRDF
  Chairman of TPLF/EPRDF
  Served as the Prime Minister of Ethiopia
  2. Seyoum Mesfin
  Founding member of TPLF
  Freedom Fighter TPLF/EPRDF
  Long time leader of TPLF/EPRDF
  Deputy Chairman of TPLF/EPRDF
  Served as the foreign Affairs Minister

  3. Abadi Zemo
  Freedom Fighter TPLF/EPRDF
  Long time leader of TPLF/EPRDF
  4. Fisseha Afewerki
  Freedom Fighter TPLF/EPRDF
  Diplomat
  Chief, office of the President
  5. Tefera Walwa
  Freedom Fighter EPDF/EPRDF
  Served as Deputy Prime Minister
  6. General Elfatih Erwa
  7. Al Fre Ali Mirah
  8. Abdel Hamid the Pilot

  / source mekele university /

  © 2015 TIGRAY MARTYRS’ MEMORIAL MONUMENT CENTER . All Rights Reserved. Designed By JoomShaper

  Please publish modules in offcanvas position.